🔇Unmute
መቱ ፤ ሕዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ምርታማነትን በማስፋት በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን በኢሉባቦር ዞን የሁሩሙ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በወረዳው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በወረዳው በበጋ ስንዴ ከ10 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት ለማልማት መታቀዱም ተገልጿል።

በወረዳው የበጋ መስኖ ስንዴ ግብርና ከተሰማሩ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ወንድሙ ኢተፋ፣ በአካባቢያቸው ያለውን የውሃ ሀብት በመጠቀም በበጋ ስንዴ ልማት መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
ለዚህም ደግሞ የውሃ ፓምፖችን ጨምሮ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት እና ትራክተር ከወረዳው ድጋፍ ማግኘታቸውን አንስተዋል።
ይህም የስራውን ጫና ከመቀነስ ባለፈ ምርታማነትን የሚያሳድግ በመሆኑ የተሻለ ተጠቃሚ ለመሆን እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፉት አመታት ከተገበሩት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ በመነሳትም መሬታቸውን በአግባቡ ማዘጋጀታቸውን አክለዋል።

አርሶ አደር አቶ በፍርዱ በሪሶ በበኩላቸው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ ተሰማርተው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘርን ጭምሮ አስፈላጊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።
የኢሉባቦር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ፣ በዞኑ የበጋ ስንዴ ግብርናን በማጠናከር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም አርሶ አደሮች እና ወጣቶችን በማደራጀት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን በኩታ ገጠም እንዲያከናውኑ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም በዞኑ ለማልማት ከታቀደው 120 ሺህ ሔክታር መሬት 35 ሺህ ሔክታሩ በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።
በዛሬው እለትም በ10 ሄክታር መሬት ላይ ይፋዊ ዘር መዝራት መርሃ ግብር መካሄዱን ጠቅሰው በቀጣይም የታቀደውን መሬት ለማልማት ርብርቡ ይቀጥላል ብለዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026