🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 23/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ(Energy Efficiency Conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይደረጋል።
ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ 29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው።
የጥምረቱ ማዕቀፍ በአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መጽደቁ ይታወቃል።
“የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው።
አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽንና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው።
ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤታማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ራሺድ አሊ አብደላ ኮንፍረንሱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የኢነርጂ ውጤታማነት የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ዋነኛ ሀብት ነው ብለዋል።
የኢነርጂ ውጤታማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ነው።
ባለድርሻ አካላቱ በአፍሪካ ዘላቂ የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽንን ማፋጠን የሚያስችሉ ውጤታማ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ፖሊሲዎች ላይ በመምከር ለቀጣይ ስራዎች የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡ ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ሌሎች ተጓዳኝ ሁነቶች እንደሚከናወኑም ታውቋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026