🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ከለውጡ በኋላ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና ኢኒሼቲቮች የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነት በአይነትና በመጠን እንዲጨምር ማድረጋቸውን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የግብርና ሚኒስቴር የ2018/19 የመኸርና የበልግ ወቅት የሰብል ልማት ንቅናቄን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የመኸር፣የበልግና የበጋ መስኖ ልማት ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው፡፡
"ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነት በሀገር ደረጃ ማረጋገጥ" የሚል ሀገራዊ ንቅናቄ መጀመሩን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው፤የምግብና ሥርዓተ ምግብ ዋስትናን በቤተሰብና በሀገር ደረጃ ማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል፡፡
ከለውጡ በኋላ ግብርናውን በማዘመንና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የፖሊሲ ክለሳና የተለያዩ ኢንሼቲቮች ተግባራዊ መደረጋቸውን ጠቅሰው፤የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲውን ዘመኑን በዋጀ መንገድ መሻሻሉን ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡
በዚህም ከለውጡ በኋላ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችና ኢኒሼቲቮች የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነት በአይነትና በመጠን መጨመሩን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለግብርና ስራ ምቹ የሆነ የሰብል ልማት ስነ-ምህዳር ያላት መሆኑን ገልጸው፤ በክልሎች የሚገኙ ጸጋዎችን በመለየት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል።
ተኪ ምርትን በሀገር ደረጃ ማምረት፣የሥራ ዕድል መፍጠርና የውጭ ምንዛሪን የሚያሳድግ የሆርቲካልቸር መር የሰብል ምርትን ማበረታታት ስትራቴጂያዊ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ ለተመዘገበው ስኬት የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸው፤ የኩታ ገጠም እርሻ መስፋፋት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪዎች አቅርቦት ለዘርፉ ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ብለዋል፡፡
መንግስት ለአርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያን በድጎማ ማቅረብ ከጀመረ አራት ዓመታትን መስቆጠሩን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ምርጥ ዘር አቅርቦትም በየዓመቱ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026