የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በክልሉ የነዳጅ ግብይትን ህጋዊነት በመቆጣጠር የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅግጅጋ፤ መጋቢት 25/2018(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የነዳጅ ግብይትን ህጋዊነት በመቆጣጠር የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ።

የሶማሌ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ሼክ ሀሰን በሰጡት መግለጫ በመካካለኛው ምስራቅ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ የገጠመው የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ጫና በህብረተሰቡ ላይ ተጽዕኖ እንዳያደርስ ጥብቅ ቁጥጥር መደረጉን ገልጸዋል።

ለተግባራዊነቱም የቅድሚያ ቅድሚያ ነዳጅ ለሚያስፈልጋቸው ተሽከርካሪዎች፣ የኤክስፖርት ድርጅቶች፣ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች፣ የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች ተደራሽ መደረጉን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠር የክልሉ የጸጥታ ተቋማት ከፌዴራል ፖሊስና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በዚህም ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመግታት በተደረገው ጥረት 3ሺህ 500 ሊትር ነዳጅ ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርን ለመቆጣጠር በሚደረገው ቅንጅታዊ ስራ ያለውን ተሳትፎ እንዲያጠናክርም ሃላፊው ጠይቀዋል።

በክልሉ አዲሱ የነዳጅ ጭማሪ ታሪፍ መደረጉንና ህብረተሰቡ ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም የግንዛቤ ስራ እየተካሄደ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ ሌሎች ታዳሽ ሀይልን በመጠቀምና አላስፈላጊ ጉዞ በመቀነስ የነዳጅ ቁጠባውን ተግባራዊ እንዲያደርግም መክረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026