🔇Unmute
ጭሮ፤ሚያዝያ 2/ 2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ለዘንድሮው የትንሳኤ በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ።
እንደ ነጋዴዎቹ ገለጻ፤ ለበዓሉ የሚሆኑ የእርድ ሰንጋዎች፣ ፍየሎችና ዶሮዎች በስፋት ለገበያ ቀርበዋል።
በእንስሳት ንግድ የተሰማራው ወጣት አሊ መሐመድ እንደገለጸው፤ ለበዓሉ የሚሆኑ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ሰንጋዎች በየዋጋ አማራጫቸው ቀርበዋል።
በተለይም የእንስሳት አቅርቦት ምንጭ ከሆነው የገለምሶ አካባቢ በቂ ምርት በመኖሩ፣ ለሸማቹ የሚፈልገውን ያህል ማቅረብ መቻሉን ተናግሯል።
ሌላኛው ነጋዴ አቶ ጋዲሳ ደመቀ በበኩላቸው፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ሰንጋዎችን በተለያየ መጠንና ዋጋ ለገበያ ማቅረባቸውን አረጋግጠዋል።
በገበያው ላይ የሚታየውን የዋጋ ሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ዋሲሁን ጎሳ፣ ከአቅርቦት አንጻር ችግር ባይኖርም መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ጠቁመዋል።
እንደ በሬው ሁኔታ ዋጋ ቢለያይም ለበዓሉ የተሻለ አቅርቦት መኖሩን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የፍየል ገበያን በተመለከተ አቶ ተከተል ገዙ እንደተናገሩት፣ ባለፉት ቀናት ከነበረው ዋጋ መጠነኛ ጭማሪ ቢታይበትም አቅርቦቱ ግን ጥሩ ነው።
በአጠቃላይ በጭሮ ከተማ የትንሳኤ ገበያ ካለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ የእንስሳት አቅርቦት የተሻለ መሆኑን ነጋዴዎች እና ሸማቾች ተናግረዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026