የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ከአካባቢው የአፈር ሁኔታ ጋር በማስማማት መቅረብ መጀመሩ በምርት ላይ ውጤት እያስገኘ ነው

May 15, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ፤ ግንቦት 7/2018 (ኢዜአ)፦ በአፋር ክልል የአፈር ማዳበሪያን ከአካባቢው የአፈር ሁኔታ ጋር በማስማማት መቅረብ መጀመሩ በምርት ላይ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ።

ለዘመናት በከብት እርባታ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ፣ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ወደ መስኖና ቋሚ ግብርና በስፋት እየተሸጋገረ ይገኛል።

የአፈር ለምነትን ለማሻሻልና የግብርና ስራውን የባህላዊ አሰራር ተጽዕኖ በማውጣት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም በክልሉ እየተለመደ መጥቷል።

በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የእርሻ ኢንቨስትመንትና ግብአት ዘርፍ ምክትል ኀላፊ አቶ ሃሩን ዓሊ እንደተናገሩት፤የአፈር ማዳበሪያውን ከአካባቢው የአፈር ሁኔታ ጋር በማስማማት ማቅረብ መጀመሩ ምርትን በማሳደግ ላይ ትልቅ መሻሻል አሳይቷል።

በበጀት ዓመቱ 50 ሺህ ኩንታልየአፈር ማዳበሪያ ለማስገባት ታቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በእስካሁኑ እንቅስቃሴ 48 ሺህ 800 ኩንታል ቀርቦ በጋሊኮማና ደንከሊያ ዮኒየኖች አማካኝነት በመሠራጨት ላይ መሆኑም ተመላክቷል።

በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ አጠቃቀም በይፋ መጀመሩን ተከትሎ፣ በተለያዩ የአዝዕርት፣ የፍራፍሬና የአትክልት ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የምርት ጭማሪ መታየቱን ገልጸዋል።

ይህ ስኬትም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችና የተመዘገቡ መሻሻሎች ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በአፋር ክልል የተከናወኑ የግብርና ስራዎች፣ በረሃማ አካባቢዎችን ማልማት እንደማይቻል ይታመንበት የነበረውን የተዛባ ትርክት የቀየሩና ማንኛውንም ሰብል ማምረት እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የግብዓት አቅርቦቱ ብቻውን ስኬታማ ሊሆን እንደማይችል የጠቀሱት አቶ ሃሩን፣ ማዳበሪያው በአግባቡና በሳይንሳዊ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል የእያንዳንዱ አርሶ አደር ማሳ በባለሙያዎች እንዲታገዝ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ይህም አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ከቴክኖሎጂው ተገቢውን ውጤት እንዲያገኝና የምርት ብክነትን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026