🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት የዘርፉ የሰው ኃይል ልማትና ፈጠራ ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ገለፁ።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወቃል።
ስትራቴጂው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ የ5ጂ ኔትወርክን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ማድረግ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ማስፋፋት እና ዜጎችን በዲጂታል ክህሎት ማሰልጠን ላይ ያተኩራል።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የፈጠራ ስራዎችን ለማፋጠንና የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት ለማበልፀግ አስተዋፅኦ አላቸው።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች እንዳሉት፤ ዲጂታላይዜሽን ለማሳለጥና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግቦችን ለማሳካት በሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት እየሠሩ ነው።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር)፤ ለዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ መደላድል ፈጥሯል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት አሰጣጥን በመከተል እና ከዲጂታል ስርዓት ጋር የማስተሳሰር ስራ እየተሰራ ነውም ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የዲጂታላይዜሽን ትግበራውን ለማሳለጥ በሰው ኃይል ልማት ላይ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው ባለው የፈጠራ ማጎልበቻ ማዕከል በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ያተኮሩ የፈጠራ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ውጤታማነት የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ውጤታማነት የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን አውስተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራን ለማሳለጥ በሰው ኃይል ልማት ላይ እየሰራ መሆኑና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሳይበር ሴኪዩሪቱ የትምህርት መርሃግብሮችን ማስተማር መጀመሩን ተናግረዋል።
ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጋር የተያያዙ የትምህርት መርሃግብሮች ለመክፈት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የዩኒቨርሲቲው የ5 ሚሊየን ኮደሮች ለማፍራት የተያዘውን ግብ ለማሳካት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ታፈሰ ማቲዎስ(ዶ/ር) ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው አብዛኛውን አሰራሩን ዲጂታላይዝ ማድረጉን ገልፀው፤ ዩኒቨርሲቲው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026
አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እን...
Jul 24, 2026
ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ...
Jul 23, 2026
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2018 ( አዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።...
Jul 16, 2026