የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በኩታገጠም አሠራር ካለማነው የስንዴ ሰብል የተሻለ ምርት እየጠበቅን ነው -አርሶ አደሮች

Jun 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሮቤ ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በባሌ ዞን በበልግ አዝመራ በኩታገጠም አሠራር ካለሙት የስንዴ ሰብል የተሻለ ምርት እየጠበቁ መሆኑን የሲናና ወረዳ አርሶ አደሮች ገለጹ።

በዞኑ በበልግ ወቅት በተለያዩ ሰብሎች ከለማው ከ277 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

የሲናና ወረዳ አርሶ አደር የሆኑት አቶ አደም ሁሴን እንዳሉት፤ በዘንድሮው የምርት ወቅት ምርጥ ዘርና የተሻሻሉ የግብርና ፓኬጆችን በአግባቡ በመጠቀማቸው ከአንድ ሄክታር እስከ 65 ኩንታል ምርት እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ባለፉት አራት ዓመታት በኩታገጠም አሠራር በመሳተፍ በሚያገኙት ገቢ የቤተሰባቸውን ኑሮ እንደቀየረውም አክለዋል።

ሌላው የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር አቶ አህመድ በከር በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል በባህላዊ መንገድ ከአንድ ሄክታር ያመርቱ የነበረው የስንዴ ምርት ከ20 ኩንታል እንደማያልፍ አስታውሰዋል።

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተሻሻሉ አሠራሮችን የመጠቀም ዝንባሌና ተግባሩም እየተሻሻለ በመምጣቱ ከአንድ ሄክታር ማሳ እስከ 60 ኩንታል የስንዴ ምርት ማምረት ላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል።

በዘንድሮ የምርት ወቅት በተለይ በባለሙያዎች ምክር የታገዘ የፓኬጅ አጠቃቀም፣ በሽታን መቋቋም የሚችል ምርጥ ዘር በወቅቱ በመጠቀማችን የማሳችን ቁመና እጅግ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ የተሻለ ምርትም እንጠብቃለን ነው ያሉት።

የሲናና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የመሬትና ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደበሌ ሐቤቤ እንደገለጹት፤ በወረዳው በበልግ ወቅት በኩታገጠም ከለማው 45 ሺህ ሄክታር የስንዴ ማሳ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።


የአርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደግ ለምርታማነቱ መጨመር ዋነኛ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የባሌ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሙአዊያ ፉአድ በበኩላቸው፤ በዞኑ የነበረው የዝናብ ስርጭት ለሰብል ልማቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል።


በበልግ አዝመራ በተለያዩ ሰብሎች ከለማው ከ277 ሺህ ሄክታሩ የታቀደውን የ8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት የሚያግዙ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026