የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሰኔ 17 እና 18 በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Jun 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ሰኔ 9/2018 (ኢዜአ)፡-የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ሰኔ 17 እና 18 በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኮንፈረንስ ዝግጅትን አስመልክተው የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዝደንት ብርሀኔ በየነ (ዶ/ር) ኮንፈረንሱ የአፍሪካን የሳይበር ደህንነት አቅም፣የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር እና በአህጉሪቱ በፍጥነት እየተስፋፋ ባለው የዲጂታል ሽግግር መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀምን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በርካታ የአፍሪካ ተቋማት የሳይበር ደህንነት አቅማቸውን እያጠናከሩ ቢሆንም፣ በአተገባበር፣ በቅንጅት፣በክህሎት ልማት እና በመቋቋም አቅም ላይ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው ጠቁመዋል።

ይህንንም ለመፍታት የላቀ ትብብር እና የእውቀት መጋራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

ኮንፈረንሱ ልምዶችን ለመለዋወጥ፣በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲዎችን ለማሳወቅ፣ የአፍሪካን የፈጠራ ስራዎች ለማሳየት፣ የሳይበር ዝግጁነትን ለማሻሻል እንዲሁም ቀጠናዊ የሳይበር መቋቋም አቅምን እና የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማራመድ እንደሚያግዝ አመላክተዋል።

በተጨማሪም የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ተቋማትን፣ተቆጣጣሪ አካላትን፣ አካዳሚዎችን እና የንግድ ተቋማትን በአንድ ላይ የሚያገናኝ መሆኑን አንስተዋል።


የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የዲጂታል መረጃ ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት አገልግሎት ክፍል ኃላፊ አሞስ ሞሞድዛ በበኩላቸው፥ ሀገራት የዲጂታል ሽግግር ጉዟቸውን እያፋጠኑ እንደሚገኙ ገልጸው መንግስታት የህዝብ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል እየቀየሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የሳይበር ደህንነት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሳሰሩ መምጣታቸውን አንስተዋል።

ምርታማነትን እና ፈጠራን ሊያሻሽሉ የሚችሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎቶች የረቀቁ የሳይበር ጥቃቶችን ለመሰንዘር፣የቪዲዮ እና የድምጽ ማጭበርበሪያዎችን ለመፍጠር፣መረጃን ለመቀልበስ እና መሰል የደህንነት ስጋቶችን ለማባባስ ሊውሉ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

በመሆኑም የሳይበር ደህንነት አቅሞች ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሊጎለብቱ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በኮንፈረንሱ ቀናት የሳይበር ደህንነት አቅምን እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በኃላፊነት፣ደህንነቱ በተጠበቀ እና ሁሉንም ባካተተ መልኩ እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻል ምክክር ይደረግበታል ብለዋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት አስተዳደር፣ በአስተማማኝ የዲጂታል ሽግግር፣ በቁልፍ መሰረተ-ልማት ጥበቃ፣ በሳይበር መቋቋም አቅምና በክህሎት ልማት ላይ እንደሚያተኩሩ ጠቁመዋል።

አፍሪካ የንግዱን ማህበረሰብ እና የተጠቃሚዎችን ፍላጎት የሚያሟሉ አዋጭ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት፣በመለየት እና በመተግበር የሰው ሰራሽ አስተውሎት የወደፊት ዕጣ ፈንታን በንቃት መቅረጽ እንዳለባት አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026