የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በወላይታ ዞን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

Jul 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ ፤ ሰኔ 24/2018(ኢዜአ)፦ በወላይታ ዞን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የግብር አሰባሰብ ሂደትን በመጠቀም ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ‎ከዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ጋር በመተባበር የ2018 ዓ/ም የግብር ዘመን የታክስ አሰባሰብና የ2019 የንግድ ፈቃድ ዕድሳት ንቅናቄ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።


በመድረኩ የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ በዘንድሮ በጀት ዓመት 5 ነጥብ 51 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድረስ 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

ይህም አፈፃፀሙን 95 በመቶ ማድረሱን አንስተው ተግባሩ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰቡ ዲጂታል የተደገፈው አሰራርና የባለሙያዎች ቁርጠኝነት የተሻለ ገቢ እንዲሰበሰብ ማገዙን አስረድተዋል።

ከመረጃ አያያዝና ትንተና ጀምሮ በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በጋራ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል።

ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ የግብር ዘመኑ የታክስ አሰባሰብና የንግድ ፈቃድ ዕድሳት እንደሚጀመርም ገልጸዋል።


‎የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ታዴዎስ በበኩላቸው ዞኑ በተለያዩ ዘርፎች የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ውጤቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ‎ተቀናጅተው በመስራታቸው የመጣ መሆኑን በማንሳት ቀጣይ የህዝቡን አዳጊ የልማት ፍላጎት ለማሟላት የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን በማዘመን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

የ‎ዞኑ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ እንቅፋት የሆኑ እንደ ህገወጥ ንግድና ያለደረሰኝ የሚደረገውን ግብይት በቁርጠኝነት መቆጣጠር እንደሚገባም አሳስበዋል።

የንቅናቄ መድረኩ ዓላማም የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እና የንግድ ስራ ፈቃድ ዕድሳት ተግባርን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ምክክር ለማድረግ መሆኑንም አስረድተዋል።

በመድረኩም የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በወላይታ ዞን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ወላይታ ሶዶ ፤ ሰኔ 24/2018(ኢዜአ)፦ በወላይታ ዞን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የግብር አሰባሰብ ሂደትን በመጠቀም ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የ...

Jul 3, 2026

ምክር ቤቱ ሦስት አዋጆችን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23/2018 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስና የኢትዮጵያ ካርበን ገበያ ...

Jul 1, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቋቋሙ የግብይት ማዕከላት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት ፈጥረዋል

ሆሳዕና ፤ሰኔ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተቋቋሙ የግብይት ማዕከላት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት የተረጋጋ የገበያ ስርዓት እየ...

Jun 30, 2026

በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ሊጠናከር ይገባል 

ጋምቤላ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለተያዘው ግብ መሳካት፣ የባለድ...

Jun 26, 2026