🔇Unmute
ደሴ ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):-በደሴ ከተማ ባለፉት አምስት ዓመታት በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰሞኑን መስጠታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ላይም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
ይህንኑ ማብራሪያ አስመልክቶ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በከተማው ባለፉት አምስት ዓመታት በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ጫኔ መንገሻ በሰጡት አስተያየት፤ ባለፉት ዓመታት በደሴ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ከተማዋን ያዘመኑ ናቸው ብለዋል።
በከተማዋ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል እንዲሁም በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ትውልድ ተሻጋሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ዘሪሁን ማንደፍሮ በበኩላቸው፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢያቸው የተገነባው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት የአካባቢውን ቱሪዝም በማነቃቃት ለደሴ ከተማና ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን፣ የአገልግሎት ዘርፉን ማሳደጉን በምሳሌነት አንስተዋል።
በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የተናገሩት ደግሞ የደሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ፈረጃ ሱሌማን ናቸው።
በተለይ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የእናቶችን ተጠቃሚነት ያሳደጉ ናቸው ያሉት ወይዘሮ ፈረጃ፤ የኮሪደር ልማት፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ መጀመርና ሌሎች የልማት ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ነዋሪዎቹ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የተጀመረው ልማት ዳር እንዲደርስ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026