የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ ግቦች እንዲሳኩ ከአባል ሀገራት ጋር በትብብር መስራቷን ታጠናክራለች

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ቀጣናዊ ግቦች እንዲሳኩ ከአባል ሀገራት ጋር በትብብር መስራቷን እንደምታጠናክር የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ።

የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር 22ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።


የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ገበያውን ወደ ሥራ ለማስገባትና የትስስሩን ተቋማዊ እድገት ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ጠቅሰዋል።

ትስስሩን ለመምራት ኢትዮጵያ በሊቀ-መንበርነት መመረጧን አስታውሰው፤ የተጀመሩ ቀጣናዊ ጥረቶችን ለማስቀጠል ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ የትስስሩን በተቋማዊ ታማኝነት፣ በቀጣናዊ አንድነትና በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ የተቀናጀ ገበያ የመፍጠር የጋራ ግብን ለማሳካት ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር ትብብሯን እንደምታጠናክር አመልክተዋል።

የጋራ ቁርጠኝነትን በማጉላት፣ ለአባል ሀገሮች ሁሉ ጥቅም ሲባል ድርጅታችንንም ሆነ ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ገበያችንን ለማጠናከር የተገኘውን መልካም አጋጣሚ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።


የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ደኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳን ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ሚናዋን እየተወጣች ነው ብለዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ማዕቀፍም ቀጣናውን በኃይል የማስተሳሰር ሚናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ በአባል ሀገራቱ መካከል በጋራ ለመስራት የተደረሱ ስምምነቶች እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ውሎችን ጨምሮ በተለያዩ አሰራሮች ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ገበያ ማዕከሉ ቦታ ለመወሰን ሌላው የጉባኤው ዋና የውይይት አጀንዳ መሆኑን ገልጸዋል።


የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር 13 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን፤ በአባል ሀገራቱ መካከል የኤሌክትሪክ ኃይልን በጋራ ለመጠቀም፣ የኃይል ግብይት ለማካሄድ እና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ታልሞ የተመሠረተ ነው።

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ሊቢያ የትስስሩ አባል ሀገራት ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026