የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Jul 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የ2026ቱን የአፍሪካ የትምህርት ኢኖቬሽን ኤክስፖ በመጪው ሐምሌ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ኤክስፖ፤ “በትምህርት ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን ማፋጠንና ለአፍሪካ የክህሎት ዘመን የአዳዲስ መፍትሔዎችን ተደራሽነት ማስፋት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ታውቋል።

ይህ አህጉራዊ ኤክስፖ በአፍሪካ የትምህርትና ክህሎት ሥርዓት ውስጥ ያሉ የጥራት፣ የተደራሽነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ክፍተቶችን በቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመፍታት ያለመ ነው።

መድረኩ በተለይም አዳዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማስተዋወቅ የአፍሪካን የትምህርት ዘርፍ ማዘመን በሚቻልባቸው ስትራቴጂዎች ላይ ይመክራል።


በኤክስፖው በትምህርት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በሮቦቲክስ ዘርፎች ከፍተኛ ተፅዕኖ ማምጣት የቻሉ ከ20 በላይ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።

በተጨማሪም በዲጂታል ትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በአረንጓዴ ክህሎቶች፣ በምርምርና በኢንዱስትሪ አጋርነት ላይ ያተኮሩ ውይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ውይይቶቹም ከአህጉራዊ የትምህርትና የሳይንስ ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኤክስፖው ከ300 በላይ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ የፈጠራ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮች እና የቴክኖሎጂ መሪዎች በአካል እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ታዳሚዎችም በበይነ መረብ አማካኝነት በሁነቱ ላይ እንደሚሳተፉ ኢዜአ ከአፍሪካ ኅብረት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ኤክስፖው በአጠቃላይ በአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የዲጂታልና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀም ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።

ይህም አፍሪካ ለቀጣይ የኢኮኖሚ ሽግግር ብቁና ዝግጁ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንዲሁም የአህጉሪቱን የሰው ኃይል አቅም ለማጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላት ታምኖበታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026