🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 5 /2018 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ የገበያና የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን የሚያሳልጥ የግብይት ሥርዓት መፈጠሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ የከተማ አስተዳደሩን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው።
ከንቲባዋ በገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነት ቅነሳ ሪፖርታቸው፤ በመዲናዋ የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን የሚያሳልጡ ስትራቴጂክ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልጸዋል።
በዚህም በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ፣ የ8.2 ቢሊዮን ብር በጀት ድጎማ በማድረግ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።
የድጎማ በጀቱም ነዋሪዎች ቀጥተኛ እፎይታ በሚያገኙባቸው የሕዝብ ትራንስፖርት፣ የጤና መድህን፣ የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቤት ምገባ፣ ለዳቦ ምርትና ለሌሎች መሠረታዊ ምርቶች እንዲውል መደረጉን አንስተዋል።
ኅብረተሰቡም የምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ስኳር፣ ዘይትና መሰል መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።
በ15.9 ቢሊዮን ብር ወጪ የምርት ማከማቻ፣ የጅምላና የችርቻሮ መሸጫ ሱቆችን ያካተቱ ሰባት ዘመናዊ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት በአምስቱም የከተማዋ መግቢያ በሮች ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቁመዋል።
የአማራጭ ገበያ ተደራሽነትን ለማስፋፋት ባለፉት አምስት ዓመታት የተጀመረው የቅዳሜና እሁድ ገበያ፣ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ወደ 259 ማሳደግ እንደተቻለ አስታውቀዋል።
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና መርሃ ግብር አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች የዕለት ተዕለት የምግብ ፍጆታቸውን በራሳቸው የማሟላት አቅም እንዲኖራቸው እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026