የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ

Jul 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀረር ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት አመት 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ አመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ከክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ የቀረበለትን የክልሉን የ2019 በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አጽድቋል።

የበጀት ረቂቁን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ ናቸው።

ከበጀት ድልድሉ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው የካፒታል በጀት ሲሆን፤ ይህም 65 በመቶ ድርሻ ያለው እንደሆነ ተገልጿል። እንዲሁም 35 በመቶው ለመደበኛ ወጪ ተመድቧል ።

በጀቱ የክልሉን የልማት ፍላጎት ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተመደበ መሆኑን ጠቁመው በተለይም በ2018 የበጀት አመት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንዲሁም በገጠርና በከተማ የሕዝብን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ሊመልሱ በሚችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ለገጠር እና ለከተማ ኮሪደር ልማት፣ ለንፁህ መጠጥ ውሃ፣ ለትምህርትና ጤና ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎች በተሳለጠ መንገድ ለማካሄድ የሚያስችል በጀት መሆኑንም አመልክተዋል።

ምክር ቤቱም በቀረበው የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ አጽድቋል።

በቀጣይም ምክር ቤቱ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች፣እቅዶችና ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026