🔇Unmute
ሉሜ፤ ሐምሌ 11/2018(ኢዜአ)፦ በገጠር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ በመቀየር ዘመናዊ ህይወት እንዲመራ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የጨፌ ኦሮሚያ አባላት ተናገሩ።
የጨፌ ኦሮሚያ አባላት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ደከቦራ ካራና ቱሉ ሬኤ ቀበሌ የሐሮሜ የመንደር ልማትን ጎብኝተዋል።

ከጨፌው አባላት መካከል አቶ ኃይሉ ዲሳ እንደገለፁት፤ የአርሶ አደሩን ህይወት ለማሻሻልና ለመለወጥ የተጀመረው የሐሮሜ መደር ልማት ጥሩ ጅምር ላይ የሚገኝ ነው።
የሐሮሜ መደር ልማት ስራ በአንድ ቦታ ላይ የተሟላ መሰረተ ልማት እንዲኖር መደረጉ አርሶ አደሩ ዘመናዊ ህይወት እንዲመራ ተጠቃሚቱ እንዲረጋገጥ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘመናዊ መንገድ የእንስሳትና የሰው መኖሪያን የለየ፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድና ኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት መቻሉ የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ በእጅጉ እንደሚቀይር ነው የገለጹት።

አርሶ አደሩ የተሻለ ህይወት እንዲኖር መስራት የቤተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተቀመጠውን ግብ የሚያሳካ መሆኑን የገለጹት ዴግሞ ሌላው የጨፌው አባል አቶ ሁሴን ጉቱ ናቸው።
በሐሮሜ መንደር ልማት የታየው ትልቅ ለውጥ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተስፋፍቶ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
በተለይ አርሶ አደሩ ዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ዘዴ እንዲከተልና የተሟላ የመሰረተ ልማት ፓኬጅ በአንድ ቦታ እንዲያገኝ መደረጉ የአኗኗር ዘይቤውን ማሻሻል ያስቻለ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የሉሜ ወረዳ አስተዳዳሪ ድሪባ ቶሎሳ በበኩላቸው፤ በወረዳው በሶስት ቀበሌዎች የሐሮሜ መንደር ልማት መጀመሩን ጠቁመዋል።

በቱሉ ሬኤና ደከቦራ ካራ ቀበሌን ጨምሮ የሐሮሜ መንደር ልማት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው በደከቦራ ካራ ቀበሌ ስድሳ የሐሮሜ መንደር በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በመንደር ልማቱ አርሶ አደሩ የኤሌክትሪክ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድ፣ የገበያ ማዕከል፣ የነዳጅ ማደያዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በአንድ ቦታ እንዲያገኝ መደረጉንም ነው የገለጹት።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳደሪ ጉታ ገዳ በበኩላቸው፤ በዞኑ ከሚገኙ 13 ወረዳዎች መካከል በ7ቱ ዘመናዊ የሐሮሜ መንደር ልማት መጀመሩን አስታውቀዋል።
በተለይ በሉሜ እና አዳኣ ወረዳዎች ደከቦራ፤ ካራ፣ ቱሉ፣ ሬኤና ጎዲኖ ቀበሌዎች ላይ እየተገነባ ያለው የሐሮሜ መንደር ልማት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አርሶ አደሩ ህይወቱን ለመለወጥና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን ለመከተል በፈቃደኝነት የሐሮሜ መንደር ልማት ውስጥ መግባቱን አስታውቀዋል።
ለእያንዳንዱ አርሶ አደር በ500 ካሬሜትር ላይ ያረፈ የተሟላ መሰረተ ልማት ያለውና ለተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎች አመቺ የሆነ ዘመናዊ መኖሪያዎችን ማካተቱን ነው ያመለከቱት።
የዞኑ መስተደድር የቤቶች ዲዛይን ጨምሮ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶችን መሸፈኑን ጠቁመው አርሶ አደሩ የቤቱን ግንባታ ወጪውን በራሱ መሸፈኑን ተናግረዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026