የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በዞኑ 487 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ዘር ተሸፍኖ እየለማ ነው 

Jul 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ገንዳውኃ፤ ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፦በምዕራብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅቱ እስካሁን 487 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ዘር ተሸፍኖ እየለማ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ጤናው ፋንታሁን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በ2018/19 ምርት ዘመን መኸር ወቅት ለሰብል ልማቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።


​በምርት ወቅቱ ከ529 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ12 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን በተደረገ ጥረት 487 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ዘር ተሸፍኖ እየለማ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ ከ370 ሺህ ሄክታር በላዩ በትራክተር ታርሶ የተዘራ መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲሁም ከ250 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም የለማ መሆኑን አመልክተዋል።

ከተዘሩ ሰብሎች ውስጥም ገበያ ተኮር የሆኑ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ጥጥ፣ ቦሎቄና ሌሎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል።


በምርት ወቅቱ ለወጭ ንግድ፣ ለኢንዱስትሪ ግብአትና ለአካባቢ ገበያ የሚሆኑ ሰብሎችም በስፋት እንደሚለሙ ተናግረዋል።

በዞኑ በእርሻ ኢንቨስትመንት የተሰማሩት አሊ መሐመድ ፤ 60 ሄክታር መሬታቸውን በሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ሌሎች ሰብሎች በዘር መሸፈናቸውን ገልጸዋል።

መሬታቸውን በትራክተር ደጋግመው በማረስ በመዝራታቸው ድካምና ወጪ የቀነሰላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

አርሶ አደር ደጀኔ ታደሰ በበኩላቸው፤ ኩታገጠም ማሳቸውን በሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ማሽላ ዘር መሸፈናቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ በ2017/18 ምርት ዘመን መኸር ወቅት ከ510 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ከመምሪያው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026

በዞኑ የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ለማሰገባት አስችሏል

አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እን...

Jul 24, 2026

 በዞኑ እየተካሔደ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ...

Jul 23, 2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2018 ( አዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።...

Jul 16, 2026