🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከሰዎች ለሰዎች ድርጅት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ አስጀምረዋል።
የስማርት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታው ሲጠናቀቅ ወጣቶችን በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ፣ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ፣ በኮሙዩኒኬሽንስ፣ በቴክስታይል እና የሲኤንሲ (CNC) ቴክኖሎጂዎች ላይ ተግባር ላይ ያተኮረ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ሥልጠና እንደሚሰጥ ከንቲባዋ ገልጸዋል።
ሀገርን ማልማት እና ከድህነት መላቀቅ በንድፈ ሐሳብ ብቻ በተገደቡ ትምህርቶች ማሳካት ስለማይቻል፣ ሐሳብን የሚያፈልቁ አዕምሮዎችን እና የሚሠሩ እጆችን ያጣመረ ክህሎት መር የሰው ኃይል እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል።

ዛሬ ያስጀመርነው ፕሮጀክት በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ወጣቶቻችንን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት፣ ከንድፈ ሐሳብ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር፣ አዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር የክህሎት ድልድይ የሚሆን ነው ብለዋል።
የዚህ ኮሌጅ ግንባታ በጥራትና በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ በልዩ ትኩረት የምንከታተለው ይሆናልም ነው ያሉት።
ፕሮጀክቱን በትብብር የሚገነባው የረጅም ጊዜ የልማት አጋር የሆነው ሰዎች ለሰዎች ድርጅት እና የሚሠራው ለትውልድ የሚሻገር ዐሻራ ነው በማለት መሬታቸውን ለፕሮጀክቱ የለቀቁ አርሶ አደሮችንም አመስግነዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026