የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ዩኒቨርሲቲው በሁለት ዓመት ምርት የሚሰጡ 13 የቡና ዝርያዎችን በምርምር በመለየት ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ ነው

Jul 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ዓመት ውስጥ ምርት የሚሰጡ 13 የቡና ዝርያዎችን በምርምር በመለየት ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ መሆኑን ገለጸ።

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አብርሃም ሹምቡሎ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርታማነትን ለማረጋገጥና ዘርፉን ለመደገፍ ጥናትና ምርምር ሲያደርግ ቆይቷል።


ዩኒቨርሲቲው ሁለት የምርምር ማዕከላትን በማቋቋም የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የምርምር ተግባራት ውጤታማ ስራ መስራቱን ተናግረዋል።

በዚህም በሁለት ዓመት በመድረስ ምርት ለመስጠት የሚችሉና ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ 13 የቡና ዝርያዎችን መለየት መቻሉን አስረድተዋል።

በምርምር የተረጋገጡትን የቡና ችግኞችን ለይቶ በማፍላት፣ ቡና አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩ አርሶ አደሮች ማሰራጨት መጀመሩንም ገልጸዋል።

በዚህም በሁለት ዓመት ከ160 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በማሰራጨት ከ40 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተው፣ በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በችግኝ ተከላ እየደገፉ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲው የቡና ምርምር በሚያካሄድባቸው ሁለት ማዕከላት የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ዳይሬክተሩ አክለዋል።

በ2019 በጀት ዓመትም የሠራተኞችን ቁጥር እና የማፍላት አቅምን በማሳደግ ለደጋ፣ ወይናደጋና ቆላማ አየር ንብረት ተስማሚነታቸው በምርምር የተረጋገጡ ከ200 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን ለማፍላት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።


የዳሞት ጋሌ ወረዳ አርሶ አደር ዳመነ ኃይሌ ነባር የቡና ዛፍን ከማሳቸው በማንሳት በምርምር በተገኙ ችግኞች እየተኩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አምና ጄ-19 እና ጄ-21 የተሰኙ ሶስት ሺህ የቡና ችግኞች እንደተከሉ የተናገሩት አርሶ አደሩ ዘንድሮም ሁለት ሺህ ችግኞችን መትከላቸውን ጠቁመዋል።

ሌላኛው አርሶ አደር አቶ ጎጆሌ ጎዴቦ በበኩላቸው አምና ሃምሳ የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን በመቀበል በማሳቸው የማላመድ ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የተተከሉ ችግኞችም የመፅደቅ መጠናቸው ከፍተኛ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸው ዘንድሮም በተመሳሳይ ሃምሳ ዝርያቸው የተሻሻለ የቡና ችግኞችን ለመትከል የማሳ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ነባር የቡና ዝርያዎችን ከዩኒቨርሲቲው በተቀበሏቸው የተሻሻሉ ዝርያዎች እየተኩ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ አርሶ አደር መምህር መስፍን ካሳ (ዶ/ር) ናቸው።

አምና ከዩኒቨርሲቲው ያገኙትን 800 «ቆቲ»፣ «አንጋፋ» እና «ጥያቴ» የተሰኙ የቡና ዝርያ ችግኞችን መትከላቸውን ጠቅሰው፣ ዘንድሮም ተግባሩን በማስቀጠል ተጨማሪ 200 ችግኞችን ለመትከል አቅደው እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በማዕከሉ በሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑት ወይዘሮ ሙሉነሽ ሻንካ እና ወይዘሮ ሙሉነሽ ሲላስ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም በአነስተኛ ሥራ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ይመሩ እንደነበር አስታውሰዋል።


አሁን ግን በምርምር ማዕከሉ በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል የተሻለ ተከፋይ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም ማገዝ መጀመራቸውንና ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026