የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የግብርና ምርትና ምርታማነት እድገት የምግብ ሉአላዊነት እንዲረጋገጥ እያስቻለ ነው

Aug 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ፤ ሐምሌ 28/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርና ምርትና ምርታማነት እድገት የምግብ ሉአላዊነት እንዲረጋገጥ እያስቻለ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ እንዲሁም በቀቤና ልዩ ወረዳ ኩታ ገጠም የበቆሎ እርሻዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


​ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በክልሉ የግብርና ሜካናይዜሽንና የኩታ ገጠም እርሻ የግብርና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል ።

ለዚህም ለአርሶ አደሩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና የግብአት አቅርቦት ተደራሽነት ላይ በቅንጅት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

የግብርና ምርትና ምርታማነት እያደገ በመምጣቱም የምግብ ሉአላዊነት እየተረጋገጠ እንዲመጣ እያስቻለ መሆኑን አመልክተዋል።


ይህም የአርሶ አደሩን ገቢ በማሳደግ የኢኮኖሚያዊ ሽግግርን ለማፋጠን የራሱን አቅም እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል።

​በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው፤ በጉራጌ ዞን በአበሽጌ ወረዳ እንዲሁም በቀቤና ልዩ ወረዳ በበቆሎ ልማት የመጣው ለውጥ የአርሶ አደሩ የግብርና ሙያተኞችን ምክር የመከተል ውጤት ነው ብለዋል።


ቢሮው ምርታማነትን ለማሳደግ የኩታ ገጠም አሰራር ተግባራዊ እንዲሆን ከመድረግ ባለፈ የምርት ብክነትን የሚቀንሱ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

የዚሁ ማሳያ የሆነው የኩታ ገጠም የበቆሎ ልማትም ሰብሉን ለመንከባከብና ዘመናዊ አመራረትን ለመተግበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በዘርፉ የመጣውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026