የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ጉልህ ሚና ይኖረዋል

Aug 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ የሳይበር ደህንነትን በማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሯ ትዕግስት ሃሚድ አዋጁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ አዋጁ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን ጠቅሰዋል።

ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ጉዞ በጠንካራ የሳይበር ደህንነት መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል መሆኑንም አንስተዋል።

የዲጂታል መታወቂያ መርሃ ግብር፣ የሞባይል ክፍያና የኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት እና መሰል ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ዳታ እንደሚያመነጩ አመልክተው፤የእነዚህን መረጃዎች እና ሲስተሞች ደህንነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የአዋጁ ወደ ስራ መግባት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የዜጎች እና የሀገርን መረጃ ከጥቃት በመጠበቅ የመረጃ ሉዐለዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አብራርተዋል።

በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ ጥቃቶች እየጨመረ መምጣት ለአዋጁ መውጣት ምክንያት መሆኑን ገልጸው፤አዲሱ አዋጅ የሳይበር ስጋትን መሰረት ያደረገ ቁጥጥር እና የተማከለ የክስተት ምላሽ ስርአትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በአዋጁ መሰረት አስተዳደሩ ቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ማሟላት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ማገዝ ፣ ለቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ የሚረዱ መመሪያዎችና ስታንዳርዶችን ማዘጋጀት በህግ ማዕቀፉ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል እንደሚገኝበት አክለዋል።

በቁልፍ መሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያ ብቁ ባለሙያና በስነ ምግባር የታነጸ የሰው ሃይል የማደረጀት ስራዎች ይሰራሉም ብለዋል።

በአዋጁ ዙሪያ ለህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራት እንደሚከናወኑም ገልጸዋል።

ቁልፍ መሰረተ ልማት ባለቤት የሆኑ ተቋማት ደግሞ የሰለጠነ ባለሙያ ማሰማራት፣ማብቃት እና ተገቢውን ደህንነት ማጣሪያ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አዋጁ እንደሚደነግግም ጠቁመዋል።

ከሳይበር ጥቃት ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉበት ቴክኖሎጂዎችን መታጠቅ ከተቋማቱ የሚጠበቅ ሌላው ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026