🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4 /2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ አስገኝቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው ብለዋል።
በዚህም ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል ነው ያሉት።
ከሁሉም በላይ ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችና ጎብኝዎች የሚገናኙበት ሥፍራ መሆን ችሏል።

ከቤተሰቦችና ሕፃናት፣ከስፖርት ቡድኖችና ከሠርግ ተካፋዮች ጀምሮ እስከ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በቦታው ይገኙበታል።
የወዳጅነት ፓርክ ከኢኮኖሚያዊ እሴቱ ባሻገር ለጤና፣ ለአካል ብቃት፣ ለመዝናኛና ለሕብረተሰብ ትስስር ትልቅ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
ይህም በጥሩ ሁኔታ የታቀዱ የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ለአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ የከተማነት ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ሰዎችን እንዴት ማገናኘት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ነው ያሉት።

ይህ ፓርክ በከተማዋ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ውስጥ እየተገነቡ ላሉ ተመሳሳይ የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ቀዳሚ ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል።
እነዚህ አዳዲስ ቦታዎች እሴት የሚፈጥሩ፣ ዕድሎችን የሚያመቻቹ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን ባለቤትነትን የሚያረጋግጡ ማዕከላት መሆናቸውን ነው የገለጹት።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026