የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት አሳድገዋል

Aug 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሴ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በከሚሴ ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 200 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሸሪፍ ቃሲም ገለጹ።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አቶ ሸሪፍ ቃሲም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በከተማዋ የተረጋጋ ሰላም እንዲኖር በማድረግ ሰፋፊ የልማት ሥራዎችን ማከናወን ተችሏል።

በዚህም አንድ ኪሎ ሜትር የኮብልስቶን መንገድ፣ ሼዶች፣ የአዳዲስ መንገዶች ከፈታና የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት በ200 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገንብተዋል።


በተጨማሪም የገበያ ማዕከልና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት በመደረጋቸው ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹና ዘመናዊ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የሕብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ዘላቂ ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

እየተፋጠነ የሚገኘው የአራት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማትም ከተማዋን በማስዋብና በማሳመር ሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደገ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።


የከሚሴ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ጣይቱ አሰፋ፤ ቀደም ሲል በከተማዋ የልማትና የሰላም እጦት ይታይ የነበረ ቢሆንም ባለፉት ዓመታት በከተማዋ የታየው የልማትና የሰላም ሁኔታ ተስፋ የጣሉበትና ያስደሰታቸው መሆኑን ተናግረዋል።


በተለይ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተከናወኑት በርካታ የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ለዚህም በጉልበታቸው፣ በገንዘባቸውና በሌሎችም መንገዶች ተሳትፎ በማድረግ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ አህመድ ጁሃር በበኩላቸው፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገነቡት የመንገድ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ሼድና መዝናኛዎች ተጠቃሚ እንዳደረጋቸው ነው የተናገሩት።


ልማቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ከመንግሥት ጎን በመሰለፍና ሰላምን በማስጠበቅ የድርሻቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026