የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በድሬዳዋ የገጠር ነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል-ቢሮው

Aug 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ)፡-በድሬዳዋ የገጠር ነዋሪዎችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን የአስተዳደሩ ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በተያዘው የመኸር ወቅት በ15ሺህ 700 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎችና ፍራፍሬዎች እየለሙ ይገኛሉ።

የአስተዳደሩ ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የገጠሩን ማህበረሰብ የምግብ ዋስትናው ለማረጋገጥ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል።

ለዚህም አነስተኛ የመስኖ እና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች በስፋት መገንባታቸውን በማሳያነት ጠቅሰው፣ ይህም አበረታች ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ወይዘሮ ሚስራ ገለጻ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በተፋሰስ ልማት ላይ የተሰሩት አበረታች ተግባራት ውሃ ገብ በሆኑ የገጠር ቀበሌዎች የመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እያገዙ ነው።

በተለይ ባለፉት ዓመታት የተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ከፍራፍሬና ከእንስሳት ሃብት ይበልጥ ተጠቃሚ እያደረጓቸው በመሆን በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ጀምረዋል ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ከ7ሺህ 700 በላይ ቤተሰቦች ወይም 56 ሺህ የገጠር ነዋሪዎች ከተረጂነት መላቀቃቸውን አስታውሰዋል።

እነዚህን ውጤታማ ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል በዘንድሮ የመኸር ወቅት 15ሺህ 700 ሄክታር መሬት በበቆሎና በማሽላ እንዲሁም በፍራፍሬና አትክልቶች መልማቱን አንስተዋል።

በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብርም ለእርሻ ሥራ በተዘጋጁ አዳዲስ ማሳዎች ላይ የፓፓያ እና የብርትኳን ፍራፍሬዎች በስፋት እየተተከሉ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በዘንድሮ ክረምት በአንዳንድ ቀበሌዎች ዝናብ በመዝግየቱ አስቀድሞ በተዘራ ዘር ላይ የደረሰን ጉዳት ለማካካስ የሚያስችሉ ልማቶች እየተከናወኑ መሆናቸወንም ወይዘሮ ሚስራ አስታውቀዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የገለፁ አርሶ አደሮች በበኩላቸው መንግስት ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ በውሃ ገብ ቀበሌዎች አነስተኛ የመስኖ አውታሮችን ተደራሽ ማድረጉን ተናግረዋል።

በዚህም ከመኸር ወቅት በተጨማሪ በበልግ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገሩ እየተጉ መሆኑን ገልጸዋል ።


የኢጀአነኒ እና የቢሻን በሄ ገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ጣሂር አብደላ እና አርሶ አደር አብደላ ሙሜ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች የከርሰ ምድር ውሃን በመጨመር የመስኖ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ።

በመስኖ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በማምረት ተጨማሪ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በዚህም የአካባቢው አርሶ አደሮች ከተረጂነት ተላቀው ወደ አምራችነት ተሸጋግረዋል ብለዋል።


የገንደሰር እና የአሰሊሶ ገጠር ነዋሪ አርሶ አደር አብዲ መሐመድ እና አርሶ አደር መሐመድ ቦሬ በአካባቢያቸው የተገነባ አነስተኛ የመስኖ አውታር በመጠቀም ፓፓያ በስፋት እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዘንድሮ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብርም ከ50 ሺህ በላይ የብርትኳን እና የፓፓያ ችግኝ ተክለው እየተንከባከቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026