ሆሳዕና፤ ታኅሣሥ 26/2017(ኢዜአ):- በግብርና ዘርፍ የሚከናወኑ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለውጤት እንዲበቁ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲጠናከር የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጠየቀ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናው ዘርፍ ያሉ ዕድሎችንና ማነቆዎችን ለመለየት የተከናወኑ ጥናቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ዛሬ ተካሄዷል።
በኢንስቲትዩቱ የምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም የምርምር ዘርፍ ዳይሬክተር ንጉሴ ዳና (ዶ/ር) እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ በስምንት የምርምር ማዕከላት የግብርናውን ዘርፍ የሚያግዙ የጥናትና ምርምር ውጤቶች እንዲፈልቁና ተደራሽ እንዲሆኑ እያደረገ ነው።
በተለይም ቴክኖሎጂን የማስረጽ ስራ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ጠቅሰው እነዚህን ጅምር ስራዎች በመደገፍ ረገድ ባለድርሻ አካላት መረባረብ አለባቸው ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ ለግብርናው ዘርፍ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ የቴክኖሎጂዎች አቅርቦትን በማመቻቸት፣ በማስፋትና በማስተዋወቅ ለተጠቃሚው እንዲደርስ የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር በበኩላቸው በክልሉ በምርምር የተገኙ የግብርና ተክኖሎጂዎች ተደራሽነት ትኩረት ማግኘቱን ገልጸዋል።
የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የግብርና ምርቶችን በአይነትና በጥራት ማምረትና ዘርፉ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠሪያ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ተረፈ፣ በክልሉ የግብርና ልማትን የሚያግዙ የጥናትና ምርምር ስራዎች በትብብር እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም በተቋሙ ስር የሚገኙ የምርምር ማዕከላትንና ንዑስ የምርምር ጣቢያዎችን በማቀናጀት በርካታ የጥናት ስራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አባላትና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025