የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

Feb 24, 2025

IDOPRESS

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።

ሚኒስትሯ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የክልሉ ገጠር ቴክኖሎጂ ብዜትና ግብርና ሜካናይዜሽን ማስፋፊያ ኤጀንሲ የሥራ እንቅስቃሴን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት ተመልክተዋል።

ሚኒስትሯ በወቅቱ እንደገለፁት ኮሌጆች የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራ እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው።

የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማዋ እየተከናወነ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ግብዓት እያመረተ መሆኑን መመልከታቸውን ጠቅስዋል።

“ኮሌጁ ማሽነሪዎችን በመጠቀም ሌሎች የፋብሪካ ውጤቶችን እያመረተ ነው” ያሉት ሚኒስትሯ፤ የኮሌጁ አሰልጣኞች በተግባር የሚያከናውኗቸው ሥራዎች ለሌሎችም ተሞክሮ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።

የገጠር ቴክኖሎጂ ብዜትና ግብርና ሜካናይዜሽን ማስፋፊያ ኤጄንሲ የግብርና ማሽነሪዎችን በማምረት ግብርናን ለማዘመን የሚያግዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በስራ ፈጠራ የራሳቸውን ገቢ እንዲያመነጩ ለሚደረገው ሂደት የሚያጠናክር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ተቋማት በቴክኖሎጂ የታገዙ እና ዘመን ተሻጋሪ ለማድረግ በፖሊሲ ደረጃ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትሯ አክለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025