የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

Feb 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በተቋሙ የሪፎርም ስራዎች፣ እየተገኙ ባሉ ውጤቶችና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅና የመከላከል አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።

ከለውጥ ስራዎቹ መካከል የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉን አስታውሰዋል።

ኮምፒውተርን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀለኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጣር የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን ጠቅሰው፣ ይህም ወንጀልን የመከላከል ሀገራዊ አቅምን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን ከደህንነት አኳያ በአግባቡ ተፈትሸው ወደ ሀገር እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ፣ ከቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ጥበቃ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል የሚችሉበት አቅም እንዲገነቡ ስልጠናዎችን በመስጠት የተሻለ የአሰራር ስርዓት እንዲኖራቸው አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅንም ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ አዋጁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በቅርቡ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል ብለዋል።

የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አቅምን ለማሳደግ በተከናወኑ ተግባራት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ደረጃ ከፍ እያለ መምጣቱን አስረድተዋል።

በዘርፉ የሰው ሃይልን ለማፍራት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ለአብነትም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ታዳጊዎች በክረምት መርሃ ግብር እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሠራ ነውም ብለዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ አስተዳደሩ ከ8 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥናትና ምርምር ዙሪያ በትብብር እየሰራም ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026