Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የወቅቱ ሊቀመንበርና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።
የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ የመጣውን ሪፎርምና የቀጣናውን ጠንካራ ግንኙነት ተከትሎ በቀጣናው አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ጥቅምት 2012 ዓ.ም መመስረቱ ይታወቃል።
የኢኒሼቲቩ ሊቀመንበርና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ኢትዮጵያ በኢኒሼቲቩ አማካይነት ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያስተሳስር የልማት ፕሮጀክቶች እየተገበረች መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለቀጣናዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ቁርጠኝነት አቋም እንዳለውም ገልጸዋል።
በዚህም ሀገሪቱ ቀጣናውን በመንገድ፣ በባቡርና በሃይልና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የሚያስተሳስሩ ድንበር ተሻጋሪ ልማቶችን በመሪነት እያከናወነች ነው ብለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት ዓመታት ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች 15 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ፋይናንስ ከልማት አጋሮች ለመሰብሰብ አቅዶ ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም ከግማሽ በላይ የሚሆነው ፋይናንስ ከልማት አጋሮች የተገኘ ሲሆን፥ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ መዋሉን ጠቅሰዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን እየተገበረች ሲሆን ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የልማት ድጋፍ ማግኘቷን አንስተዋል።
በእነዚህ ፕሮጀክቶች ከተገኙ ውጤቶች መካከልም የድርቅ መረጃ ጠቋሚ መድህን በቆላማ አካባቢዎች በስፋት ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል።
በአርብቶ አደር አካባቢዎች የተገነቡ የውሃ መሰረተ ልማቶች፣ ምርትና ምርታማነት ማሳደግን ጨምሮ 500 ሺህ ሔክታር መሬትን ከአንበጣ መንጋ ወረራ ማዳን መቻሉን ለአብነት አንስተዋል።
ኢኒቬቲቩ ኢትዮጵያ በየጊዜው እያስመዘገበች ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትና የህዝብ ቁጥር መጨመርን ተከትሎ በቀጣናው የልማት ትስስር ላይ ግንባር ቀደም ሚናዋን አጠናክራ እንድትቀጥል ያግዛታል ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በመጪው የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም 23ኛው የአፍሪካ ቀንድ አገራት የገንዘብ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች የጋራ ስብሳባ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል።
በስብሰባው ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ግምገማ የሚካሄድ ሲሆን በቀጣይም ሊተገበሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።
ኢትዮጵያን ኢኒሼቲቩን ላለፉት ሁለት ዓመታት በሊቀመንበርነት የመራች ሲሆን ከሚኒስትሮቹ ስብሰባ በኋላ የሊቀመንበርነት ስልጣኑን ለሌላ አባል ሀገር ታስረክባለች።
ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያን፣ ጅቡቲን ኤርትራን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያን፣ ሱዳንንና ደቡብ ሱዳንን ያቀፈ ሲሆን ዋነኛ ዓላማውም በቀጣናው መሰረተ ልማት ትብብርን ማጎልበት፣ የንግድና ኢኮኖሚ ውህደትን ማጠናከር የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮችን የመቋቋም አቅም መገንባትና የሰው ሃይል ልማትን ማጠናከር ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025