የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

Feb 24, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለጹ፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራር አባላት በዞኑ ተሁለደሬ ወረዳ በበጋ መስኖ የለማውን የስንዴ ሰብል ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን በጉብኝቱ ላይ እንደገለጹት ዞኑ ለስንዴ ልማት ምቹ በመሆኑ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል እየተሰራ ነው፡፡

ለዚህም በቴክኖሎጂ ታግዘው የተሻሻሉ የግብርና አሰራሮችን በማስፋት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካለፉት ዓመታት ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ ዘንድሮ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፤ የግብዓት አቅርቦቱም የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

''ቀደም ሲል ለምተው የማያውቁና ፆም ያድሩ የነበሩ አካባቢዎችን ጭምር በማልማት ምርታማነትን እያሳደግን እንገኛለን'' ብለዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ ጋሎ በበኩላቸው በቂ ግብዓት ለአርሶ አደሩ ማቅረብ በመቻሉ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ማልማት ተችሏል ብለዋል፡፡

ለበጋ መስኖ ልማት ስራው ከ27 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን ጠቁመው፤ ተገቢውን የሰብል እንክብካቤ በማድረግ፣ ከአረምና ከተባይ መከላከል መቻሉን ተናግረዋል።

በበጋ መስኖ ከለማው መሬትም ከ800 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

''አሁን ላይ በሁሉም ወረዳዎች የስንዴ ሰብል ቁመና በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል'' ያሉት አቶ አህመድ፤ አርሶ አደሩ በየቀኑ ማሳውን በማሰስና ሰብሉን በመንከባከብ ምርታማነቱን ማሳደግ እንዲችል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከአርሶ አደሩ ጋር በመግባባት በወረዳው ከ2 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ማልማት መቻሉን የተናገሩት ደግሞ የተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ካሳው ናቸው፡፡

አርሶ አደሩም ጠቀሜታውን በውል ተረድቶ በራሱ ተነሳሽነት ጭምር የመስኖ ስንዴን በማልማት በምግብ ራሱን ከመቻል ባለፈ ምርቱን በስፋት ለገበያ እያቀረበ ነው ብለዋል፡፡

በተሁለደሬ ወረዳ የ018 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ዓሊ እንድሪስ በሰጡት አሰተያየት በዘንድሮው የበጋ ወቅት ግማሽ ሄክታር ማሳቸውን በበጋ መስኖ ስንዴ አልምተው የአረምና የተባይ ቁጥጥር ሥራ እያከናወኑ ነው፡፡

ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመከተል የሰብል እንክብካቤ እያደረጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የዞንና ወረዳ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026