አዲስ አበባ ፤ጥር 3/2017 (ኢዜአ) ፦በኢትዮጵያ ጠንካራ የካፒታል ገበያ ስርዓት ለመገንባት የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በራስ አውድ መተግበር እንደሚገባ የአፍሪካ የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ገበያ ማህበር ፕሬዝዳንት ሰልስቲያን ፔሪ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ትናንት በይፋ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በተደረገ የፓናል ውይይት ላይ የአፍሪካ የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ገበያ ማህበር ፕሬዝዳንት ሰልስቲያን ፔሪ እንዳሉት በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ስራው መጀመሩ በስኬት የሚነሳ ነው።
ይህም በአገሪቱ የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለመጀመር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።
በአለም የካፒታል ገበያ ሳይኖር ውጤታማ ኢኮኖሚ መገንባት አለመቻሉን አንስተው የተለያዩ ልምዶችን መቀመርና ከሌሎች አገራት መማር እንደሚቻል ተናግረዋል።
በአፍሪካ አብዛኛው አገራት አነስተኛ ገበያ ያላቸው መሆኑን አንስተው ሆኖም ትልቅ ገበያን ለመመስረት ጠንካራ የካፒታል ገበያ ከገነቡት ልምድን መውሰድ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያም ስኬታማ ከሆኑ አገራት ጥሩ ተሞክሮን በመቅሰም ለራስ በሚጠቅም አውድ መተግበር እንደሚገባም አስረድተዋል።
ከጠንካራ ህግና መመሪያዎች በተጨማሪ የካፒታል ገበያ ላይ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲበራከቱና የህብረተሰቡን የቁጠባ መጠን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠሩ አካላት በተቀናጀ አግባብ መስራት እንዳለባቸውም ገልፀዋል።
በአፍሪካ ከጥቂት አገራት በስተቀር የባንኮች ተቀማጭ ገንዘብ በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
የቁጠባ መጠንን ማሳደግና ፕራይቬታይዜሽንን ማጠናከር ለካፒታል ገበያ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ገበያውን በሚገባ ከደገፉ በአገር ውስጥ አቅም ኢኮኖሚውን ማጠናከር እንደሚቻልም ነው የተናገሩት።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ ምጣኔ ሃብት ያላት አገር በመሆኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተጠናከረ የካፒታል ገበያ እንደሚያስፈልጋት አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025