አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017(ኢዜአ)፦የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ የኔትወርክ ማሻሻያና መልሶ ግንባታ ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።
መንግስት የአገሪቱን የኃይል አቅርቦት ከፍላጎቱ ጋር ለማመጣጠን በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የከተሜነት መስፋፋትና የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት ማደጉን ተከትሎ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል።
ለዚህም በታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረት በማድረግ ከውኃ፣ ከንፋስ፣ ከእንፋሎትና ከፀሐይ በቂ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት በመከናወን ላይ ናቸው።
በአጠቃላይ በመላ ሀገሪቱ አምስት ሚሊየን የሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን የአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ታዬ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በኃይል ረገድ አዳዲስ ደንበኞችን ተደራሽ የማድረግና ከአሌክትሪክ መስመር ርቀው የሚገኙ አካባቢዎች ደግሞ ከፀሐይ ኃይል አማራጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ለኤሌክትሪክ ተደራሽነት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች አገልግሎት እንዲሰጡ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
አብዛኛዎቹ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና መቀበያ ጣቢያዎች ቀደም ብለው የተገነቡ መሆናቸውን ተከትሎ አልፎ አልፎ ለመብራት መቆራረጥና የኃይል መዋዥቅ ምክንያት ናቸው ብለዋል።
ተቋሙ የኃይል መቆራረጥ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከልና የጥገና ስራ ከመስራቱ ባሻገር የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችንና ጣቢያዎችን መጪውን ትውልድ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የማዘመን ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በሶስት ምዕራፍ ተከፍሎ ስራው የሚከናወን ሲሆን የመጀመሪያው ምዕራፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ዋና ዋና ከተሞች በመሰራት ላይ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
ሁለተኛውና ሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ በዕቅዱ መሰረት በሀገሪቱ ትልልቅ ከተሞች የሚቀጥል ይሆናል ነው ያሉት።
በሀገሪቱ 47 ከመቶ የሚሆነው የኃይል መቆራረጥ ችግር ምክንያቱ የኤሌክትሪክ መስመር በተዘረጋባቸው አካባቢዎች በቅርብ ርቀት ባሉ ዛፎች መሆኑን አንስተው ይህንንም የማስተካከል ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆትም ለኃይል መቆራረጥ ሌላኛው ምክንያት መሆኑን አንስተው የሀገርና የህዝብን ሃብት በጋራ መጠበቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025