አዲስ አበባ፤ ጥር 4/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማትሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በ 2ኛ ዙር የጀመርናቸው ስምንቱን የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን አፈፃፀም ከማለዳ ጀምረን ተዘዋውረን ገምግመናል ሲሉ አስፍረዋል።
አብዛኛዎቹ ስራዎቻችን በተያዘላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ያሉት ከንቲባዋ ስራው በተያዘለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ 24/7 እየሰራችሁ ያላችሁ ሰራተኞች፣ እያስተባበራችሁ ያላችሁ አመራሮች፣ ቦታውን ለልማት በመልቀቅ ወደ ተዘጋጀላችሁ አዲስ ቦታ በፈቃደኝነት በመግባት የተባበራችሁ ውድ ነዋሪዎቻችን የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ ብለዋል።
እንዲሁም ማሽነሪዎቻችሁን ያለ ክፍያ ያበረከታችሁ እንዲሁም አካባቢያችሁን በማፅዳትና ህንፃችሁን በማደስ ከጎናችን የቆማችሁ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ከተማ እየገነባን በመሆኑ ሁላችሁም የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ በማለት በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025