ባህርዳር፤ ጥር 6/2017(ኢዜአ)፡-ኢትዮ ቴሌኮምና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ"ስማርት ኮርት ሲስተም" ን በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የአጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው ናቸው።
''ስማርት ኮርት ሲስተም" የክስ መዝገቦች አያያዝን ማሻሻል፣ በቪዲዮ የተደገፈ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት እንዲሁም ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ፋይል እንዲከፍቱ ዕድል የሚፈጥር መሆኑና ሌሎች የዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያሻሻል ስርዓት መሆኑ ተመልክቷል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ መንግስታዊ አገልግሎትን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ዘመኑን የሚመጥን ዲጅታል ቴክኖሎጂን መጠቀም ግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
''ዛሬ የፍትህ ስርዓትን በቴክኖሎጂ አግዘን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር የጋራ ስምምነት በማድረጋችን ደስ ብሎኛል'' ብለዋል።
''የተጣለብንን ኃላፊነት በብቃትና በጥራት ለመወጣት በቁርጠኝነት እንሰራለን'' ሲሉ ተናግረው ኩባኒያው በየተቋማቱ ለዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመን አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፤ በክልሉ የፍርድ ቤቶችን አሰራር ለማሻሻል እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ፍርድ ቤቶች ስራቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው ካልሰሩ አገልግሎትን ቀልጣፋና ተደራሽ ማድረግ እንደማይቻል ገልፀው፤ የዳኝነትና የፍትህ ስርዓቱን ቀልጣፋ ለማድረግ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተደራሽ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ለዚህም በክልሉ የሚገኙ ፍርድ ቤቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማስተሳሰር የተቀላጠፈ የዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
''የስማርት ኮርት'' አገልግሎት በተለይ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ፋይል እንዲከፍቱ ትልቅ ዕድልን ይዞ የሚመጣ ከመሆኑም በላይ የተቀላጠፈ የዳኝነት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይም የኢትዮ ቴሌኮምና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመራር አባላት ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025