
አዲስ አበባ፤ጥር 6/2017(ኢዜአ)፦በመዲናዋ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት የቱሪዝም ዘርፍን እና ሀገርን ከማስተዋወቅ ባለፈ የኢኮኖሚ ጠቀሜታቸው ከፍ ያለ መሆኑን የአዲስ አበባ የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን ፣ታሪካዊ ቅርሶችን እንዲሁም የማይዳሰሱ ትውፊቶችን በአግባቡ ለመጠቀምና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ለዚህ ስኬት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ የቱሪዝም ብራንድና ሎጎ “አፍሪካዊቷ መልኅቅ "በሚል ከሁለት አመት በፊት ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የእንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክና ወዳጅነት አደባባይን ጨምሮ ማራኪ የቱሪስት መዳረሻዎች እውን ሆነዋል።
የቢሮው ምክትል ሃላፊ ሁንዴ ከበደ እንዳሉት፤ በመዲናዋ የተገነቡት የቱሪስት መዳረሻዎችና በአዲስ እሳቤ እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከገጽታ ግንባታ ባለፈ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ እገዛ አድርገዋል፡፡
በተለይም በመዲናዋ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት የቱሪዝም እድገትን ለማሳለጥ እንዲሁም የከተማዋን ገቢ ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡
በመዲናዋ ያሉ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ማስፋት መቻሉ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያድግ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
በቱሪዝም በመዳረሻዎች አስፈላጊው መሰረት ልማት እንዲሟላ መደረጉ ለጎብኚዎች እርካታ ከመፍጠር ባለፈ ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
በተለይም በመዲናዋ የተሰሩ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች፣መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የኮሪደር ልማት ስራዎች ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ እያስገኙ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026