ጂንካ፤ ጥር 7/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከቦንድ ሽያጭ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሰባሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰብ ንቅናቄ መርሀ ግብር ዛሬ በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ ተጀምሯል።
የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ በንቅናቄ መርሀ ግብሩ ላይ እንደገለፁት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ በዞኑ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሀብት አሰባሰብ ንቅናቄ ተጀምሯል።
ከጥር 7 ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 2017 ዓ.ም ለአራት ወራት በሚቆየው የቦንድ ሽያጭ ንቅናቄ ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማሰባሰብ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
የዞኑ ህዝብም እንደ ወትሮው ቦንድ በመግዛትና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ የሀብት አሰባሰብ ስራው ውጤታማ እንዲሆን እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በንቅናቄ መርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ደሳለኝ ደጀኔ እንደገለፁት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የወደፊት ተስፋ በመሆኑ ለግድቡ የሚታጠፍ እጅ የለንም ብለዋል።
የህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ ቦንድ በመግዛትና ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው፤ አሁንም ቦንድ በመግዛት ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።
የግድቡ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድጋፋችን አይቋረጥም ያለው ደግሞ ወጣት ባንታየሁ አለሙ ነው።
ለግድቡ ግንባታ ማጠቃለያ የተጀመረውን የሀብት ማሰባሰብ ስራ በስኬት ለማጠናቀቅ ቦንድ በመግዛት እና ህብረተሰቡን በማስተባበር የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሚያዚያ ወር ወደ አሪ ዞን እንደሚደርስ የተገለፀ ሲሆን ዋንጫውን በመቀበል የሀብት አሰባሰቡ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ዝግጅት መደረጉም ተመልክቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025