አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ስድስት ወራት ከ325 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ በማጓጓዝ የተሳተፉ ኩባንያዎች 116 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በጥራት ወደ ተሳለጠ የንግድ ስርዓት” በሚል መሪ ቃል ሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በወጪ ንግድ ዘርፍ ወደ 3 ነጥብ 28 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
የጥራት መንደር ኢትዮጵያን በሚወክልና በሚያስደንቅ ደረጃ መጠናቀቁ ለሃገር ኩራት ማዕከል ሆኖ የተሳካ ስራ ነው ብለዋል፡፡
በኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥ ለንግድ ስርዓት ምቹ እንዲሆን ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸው፤ በዚህ ረገድ ብልሹ አሰራሮችን ከማረም አንጻር ህገ ወጥ ተግባር በፈጸሙ 18 የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱንም እንዲሁ።
በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት ከ2 ሚሊዮን 50 ሺህ በላይ የንግድና ምዘገባ ፍቃድ አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸው፤ ከባለፈው ዓመት ከተከናወነው 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዓመታዊ አፈጻጸም አንፃር ሲታይ በጣም ከፍተኛ አፈፃፀም መሆኑን አንስተዋል፡፡
ነዳጅ ግብይትን ስርዓት ለማስያዝ በተሰራ ስራ በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 325 ሺ ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉንና ኩባንያዎች 116 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ መደረጉን ተናግረዋል።
በሲሚንቶ ግብይት ማሻሻያ የተረጋጋ አቅርቦትና ግብይት እንዲኖር በመደረጉ ዋጋው በግማሽ መቀኑን ጠቅሰዋል።
በጨው ግብይት ሪፎርምም በጥቂት ናጋዴዎች በሞኖፖልሊ ተይዞ የነበረውን ግብይት በፍትሃዊነት ለሁሉም ክፍት መደረጉንም እነዲሁ።
የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ተቋርጦ ከነበረበት ምዕራፍ በማውጣት ወደ ንቁ ድርድር ዐውድ መግባቱን ጠቅሰው፤ ለቀጣይ 5ኛ ዙር ድርድርም ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን በማደራጀት በቂ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025