የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በምርት ዘመኑ ከተሰበሰበው የመኸር ሰብል እስካሁን 420 ሚሊየን ኩንታል ምርት ተገኝቷል- የግብርና ሚኒስቴር

Jan 22, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን ከተሰበሰበው ሰብል እስካሁን 420 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በምርት ዘመኑ 20 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑን አንስተው፤ ከዚህም 614 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።

ከአጠቃላዩ እስካሁን 18 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ላይ የደረሰ ሰብል መሰብሰቡን ገልጸው፥ ተሰብስቦ ከተወቃው ሰብል ደግሞ 420 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ገልጸዋል።

የምርት አሰባሰብ ስራው ብክነትን በሚቀንስ መልኩ በተቀናጀ ሁኔታ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተካሄደ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ዘግይተው የተዘሩ ሰብሎች የምርት ስብሰባም እንደሚከናወን አመላክተዋል።

በሌላ በኩል በሀገሪቱ የእርሻ ስራን ከዘር መዝራት እስከ ምርት መሰብሰብ የሚያዘምኑ ተግባራት እየጨመሩ መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችን የአስተራረስ ስልቶች እየተተገበሩ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለአብነትም የኩታ ገጠም እርሻ በየዓመቱ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

ለአብነትም ባለፈው የመኸር ዓመት 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ዘዴ መታረሱን ጠቅሰው በ2016/17 ምርት ዘመን ወደ 12 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማደጉን ነው ያብራሩት።

ይህም የምርት ጥራትንና ምርታማነትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025