
ደሴ፤ ጥር 13/2017(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ 158 የተለያዩ የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ዙሪያ ወረዳ ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቋል።
የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር) እንደገለጹት የክልሉ መንግስት የከርስና የገጸ ምድር ውሃን በማልማት አርሶ አደሩን በመስኖ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው።
በዚህም አሁን ላይ በክልሉ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ የ158 የተለያዩ የመስኖ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በተያዘው ዓመት 22 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቃቸውን ገልጸው፤ የ95ቱ ግንባታ ደግሞ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የመስኖ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ስራ ሲገቡ ከ26 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአዲስ መልክ በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ እንደሆኑ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በክልሉ ከ80 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ማልማት የሚችሉ 110 የመስኖ ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም በበኩላቸው የዞኑን ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ታላላቅ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዘንድሮ ዓመት ብቻ በከፍተኛ ወጪ የተሰሩ 18 የተለያዩ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተመርቀው አገልግሎት መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች እንዳሉ አስረድተዋል።
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል መሀመድ በበኩላቸው በወረዳው የጅርቲ ወንዝ ላይ 62 ሚሊዮን ብር የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ፕሮጀክቱ 200 ሄክታር የሚጠጋ መሬት በማልማት ከ700 በላይ አርሶ አደሮች በዓመት ሶስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026