የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

<p>የተደረገልንን ድጋፍ እንደ መልካም እድል በመጠቀም የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ ችለናል</p>

Feb 6, 2025

IDOPRESS

ዲላ ጥር 28/2017 (ኢዜአ):- የተደረገልንን ድጋፍ እንደ መልካም እድል በመጠቀም የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የዲላ ከተማ የልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ገለጹ።

በከተማው ላለፉት ሶስት ዓመታት በፕሮግራሙ ታቅፈው የኑሮ ደረጃቸውን ያሻሻሉ 473 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በወቅቱ የላቀ ውጤት ላስመዝገቡ ተጠቃሚዎች እውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።


እውቅና ካገኙት የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች መካከል ወይዘሮ ነጻነት ግልዶ በተሰጣቸው የገንዘብ ድጋፍ በከተማ ግብርና በተለይም በእንስሳት እርባታ ተሰማርተው ለውጥ ማምጣታቸውን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ12 በላይ የበግና የፍየል ሙክት ያላቸው ሲሆን ለገበያ በማቅረብ ኑሯቸውን ማሻሻል እንደቻሉ ጠቁመዋል።

በአካባቢ ልማት ዘርፍ ተሰማርተው ካገኙት ሳንቲም ቆጥበው በአነስተኛ ንግድ መሰማራታቸውን ያነሱት ደግሞ ሌላዋ አስተያየት ሰጭ ወይዘሮ ፀሐይ ክፍሌ ናቸው።

የንግድ ስራቸውን በማሳደግ ከ40 ሺህ ብር በላይ ተቀማጭ እንዳላቸው ጠቅሰው፤ በዚህም አራት ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንዳስቻላቸው ጠቅሰዋል።

የዲላ ከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ሥራ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ የኋላሸት ለማ "የሴፍቲኔት መርሃ ግብር በከተማ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ የከተማውን ልማት እያገዘ ነው" ብለዋል።

በተለይም አነስተኛ የመሠረተ ልማት ስራዎች፣ የአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ አረንጓዴ ልማት በተሳታፊዎቹ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን አስረድተው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።

በከተማው ላለፉት ሶስት ዓመታት በፕሮግራሙ ታቅፈው የኑሮ ደረጃቸውን ያሻሻሉ 473 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ዛሬ ራስን የመቻል ሽግግር ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

1 ሺህ 739 በሁለተኛ ዙር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ፋይናንስ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን የክህሎት፣ የሥራ ባህልና የስራ እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባታቸውንም ተናግረዋል።

በሽግግር መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የዲላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታሪኩ በየነ እንዳሉት በከተማው በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አማካኝነት በእስካሁኑ ሂደት 10 ሺህ 183 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

በሁለተኛ ዙር የፋይናንስ ተጠቃሚ የሚሆኑ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎችም በድጋፍ ያገኙትን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ በማዋል ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል።

ልማታዊ ሴፍቲኔት በክልሉ የሥራና ቁጠባ ልምድን ያሳደገ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ኢስማኤል ታደስ ናቸው።

በክልሉ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል በተከናወነ ተግባርም ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው፤ በቀጣይም ተመራቂ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን በመደገፍና በመከታተል ለተሻለ ውጤት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026