የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በድሬዳዋ የገጠሩን ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የተጀመሩ ጥረቶች አበረታች ናቸው-ከንቲባ ከድር ጁሃር

Feb 6, 2025

IDOPRESS

ድሬዳዋ፤ ጥር 28/2017(ኢዜአ) ፡-በድሬዳዋ በበልግና በመኸር እርሻ ተግባራት እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶች የገጠሩን ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ አምራችነት የማሸጋገሩን ሂደት እያገዙ መሆኑን ከንቲባ ከድር ጁሃር አመለከቱ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ዛሬ በተጀመረው የአስተዳደሩ ምክር ቤት ሶስተኛ የስራ ዘመን አራተኛ ዓመት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባዔ ባቀረቡት ሪፖርት የገጠሩን ህብረተሰብ ከተረጂነት ለማላቀቅ በመከናወን ላይ የሚገኙ ስራዎችን አብራርተዋል።

ከንቲባ ከድር በወቅቱ እንዳሉት በድሬደዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ የገጠር ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር እየተከናወኑ የሚገኙ የተቀናጁ የልማት ልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው።

በ2016/2017 የምርት ዘመን በበልግና በመኸር ወቅት ከ15 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰብል ተሸፍኖ 318 ሺህ 645 ኩንታል የማሽላና የበቆሎ ምርት መሰብሰቡን ለአብነት አንስተዋል።

የተሻለ ምርት ለመሰብሰቡ ደግሞ የተሻለ አመራር እና የተቀናጀ ድጋፍ በመደረጉ መሆኑን እንደ ምክንያት አንስተዋል።

የገጠር የአነስተኛ መስኖ ልማትን ለማጠናከር በግማሽ በጀት ዓመቱ ብቻ ከ250 ሄክታር መሬት በላይ የሚያለሙ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ በማስገባት እና ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች ከ749 ኩንታል በላይ የቡና፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርት መገኘቱን አክለዋል።

በተጨማሪም በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወተት፣ የማርና የዶሮ መንደሮች በመመስረት የገጠሩ ህብረተሰብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝና ወጣቱ የስራ ባለቤት እንዲሆን መሰራቱን ገልጸዋል።

እንደ ከንቲባ ከድር ማብራሪያ በግማሽ በጀት ዓመቱ የገጠር ህብረት ስራ ማህበራት በዘመናዊ የግብአትና ግብይት ስርዓት ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር አዳዲስ ማህበራት የማደራጀትና ነባሮቹን የማጠናከር ስራም ተሰርቷል ብለዋል።

በዚህም 3 ሺህ 470 አባላት ማፍራትና 47 ሚሊዮን 569 ሺህ ብር ተጨማሪ ካፒታል ማስመዝገብ ያስቻሉ 26 አዳዲስ ማህበራት መደራጀታቸውን ገልጸዋል።

አክለውም 105 የሚሆኑትን እንደ አዲስ የማጠናከር ስራም ተከናውኗል ብለዋል።

እነዚህን ጥረቶች አስተዳደሩ በማገዙ ማህበራቱ በግማሽ በጀት ዓመት 157 ሚሊዮን 985 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው የግብርና እና የፍጆታ ምርቶች ላይ ተሳትፈው ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻላቸውን ተናግረዋል።

እነዚህን በገጠር የተጀመሩ ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የገጠሩን ህብረተሰብ ከተረጂነት ለማላቀቅ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025