የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የንግዱ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ገዥ ትርክትን ለማጎልበት ወሳኝ ሚና አለው- ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Feb 6, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ጥር 28/2017(ኢዜአ)፦የንግዱ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከርና ገዥ ትርክትን ለማጎልበት ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጹ።

ለኢትዮጵያ ዘላቂ የሰላም ግንባታ የግሉ ዘርፍ ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄዷል።

በመድረኩ "የጋራ ትርክት ግንባታ እና ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ የግሉ ዘርፍ ሚና" በሚል የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፥ የጋራ ትርክት መገንባት ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የጋራ ትርክት በመገንባት የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ አኳያ የንግዱ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን የህብረ ብሔራዊ አንድነትና ገዥ ትርክትን ለማጎልበት ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ በበኩላቸው እንደገለጹት፥በህዝቦች መካከል ግንኙነትን ለማዳበርና አብሮነትን በማጠናከር ረገድ ንግድ ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

በሀገሪቷ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፥ይህንንም ይበልጥ ማስቀጠል እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ እያከናወነ ባለው ዘርፈ ብዙ ተግባራት የግሉ ዘርፍ ያለውን ዓይነተኛ ሚና ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በተለይም ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ከማድረግ በተጨማሪ የግጭቶች መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን አስቀድሞ ለመከላከልና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ዘላቂ ሰላምን ከማረጋገጥ አኳያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ በበኩላቸው፥በሀገሪቷ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ንግድን ለማሳለጥ ዘላቂ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህን ለማስጠበቅ የግሉ ዘርፍ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት ሃሳብም ሰላምን ከመጠበቅና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ የግሉ ዘርፍ የድርሻውን ለመወጣትም ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025