አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፡- ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ማንኛውም ሰው ራሱን የሚገልጽበትና መብቱን የሚያረጋግጥበት መለያ መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "ፋይዳ ለኢትዮጵያ" የተሰኘ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በኢትዮጵያ የነዋሪዎችን የመታወቅ መብት ለማረጋገጥ፣ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባዮች መካከል መተማመን እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና የተሳለጠ አሰራር ለማንበር የዲጂታል መታወቂያ ገቢራዊ ተደርጓል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ በአዋጅ ቁጥር 1284/2015 ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን እስካሁን 12 ሚሊዮን ያህል ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ለመሆን ተመዝግበዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዘርፍ ኃላፊ ሄኖክ ጥላሁን እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በባዮሜትሪክስ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
በዓለም ላይ አንዳንድ ሀገራት ሁለት የባዮሜትሪክስ መሰብሰቢያ መንገዶች እንዳሏቸው ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ልዩ አሰራር እንዳለም ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ የጣት አሻራ እና የአይን ብሌን አሻራ የሌላቸው አካል ጉዳተኞችን በልዩ ሁኔታ ለማስተናገድ የፊት ፎቶ እንዲወሰድ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የህግና ፖሊሲ ዘርፍ ኃላፊ ጋብሬላ አብርሃም፤ በኢትዮጵያ ማንኛውም ነዋሪ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን የሚያስችለው የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ከህፃን እስከ አዋቂ የዲጂታል መታወቂያ መውሰድ እንደሚችሉ የገለጹት ኃላፊዋ፤ አንድ ሰው ሲመዘገብ ግለሰቡ ትክክለኛ ማስረጃ ማስፈሩንና በፈቃዱ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ቅጽ እንደሚሞላ ተናግረዋል፡፡
ከአምስት ዓመት በላይ ያሉ ህፃናትም በወላጆቻቸው ፈቃድ መመዝገብ የሚችሉበት አሰራር እንዳለም ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንድሪያስ ተረፈ በኢትዮጵያ አዲስ አሰራር ሲመጣ ማህበረሰቡ ቶሎ መቀበል ላይ ውስንነት እንደሚስተዋል ተናግረዋል፡፡
ለአብነትም በቀድሞው ዘመናት ሲኒማ ቤት ሲከፈት ማህበረሰቡ መቀበል ባለመቻሉ የመጀመሪያ ሲኒማ ቤት እስከዛሬም ሰይጣን ቤት እየተባለ እንደሚጠራ አንስተዋል፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያም አዲስ ነገር ከመሆኑ አንጻር የተለያዩ አመለካከቶች ቢንጸባረቁም በህብረተሰቡ ዘንድ እየተለመደ እንደሚሄድ ጠቅሰዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ሚዲያ አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለፖሊስ ስራዎች አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፖሊስ ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር በሚያደርገው ጥረት የመታወቂያ ፎቶ እና ስም እየቀያየሩ የሚያስቸግሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ምቹ አጋጣሚ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አማካሪ ክፍሌ ገብሬ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፍቱን መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን በትክክል ለመለየት ማስቻሉን በማንሳት፤ ከ31 ሺህ የሴፍትኔት ተጠቃሚ ዜጎች 95 በመቶው ለዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል ይትባረክ በሀገሪቱ ሁሉም ነዋሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲያደርጉ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞች፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በነጻ ምዝገባ እንዲያከናውኑ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025