
አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2017(ኢዜአ)፦በሃረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ስራዎችን በምሽት ጭምር በማከናወን ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት የምሽት ስራ እንቅስቃሴዎችን የመንገድ ዳር መብራቶች፤ የአባዲር ፕላዛና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኮሪደር ልማት ስራውን በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ ስራዎችን በምሽት ጭምር የማከናወን የስራ ባህልን በማዳበር ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ለኑሮ ምቹ በማድረግ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝም አክለዋል።
በተለይ የሀረር ከተማን ገፅታ ከመቀየር ባለፈ ለበርካታ ወገኖች የስራ እድል በመፍጠር በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኮሪደር ልማቱ ለነዋሪውና ለቱሪስቶች የተመቸች ዘመናዊ ከተማን ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን በመጠቆም ስራዎችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ የምሽት ፈረቃ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።
በመስክ ምልከታው ላይ የክልሉ ካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026