አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦ ለ2017/18 የምርት ዘመን 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈፀሙን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ተከትሎ በዘርፉ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ነው።
መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ከሚሰራባቸው ጉዳዮች አንዱ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህም ለ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የማጓጓዝ ስራ በከፍተኛ ትጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በምርት ዘመኑ 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ለመፈፀም ታቅዶ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ግዥ መፈፀሙን ተናግረዋል።
የአፈር ማዳበሪያውም አምና ከነበረው አቅርቦት የአራት ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ እንዳለውም ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀዋል።
ከተገዛው 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆነው ጂቡቲ ወደብ መድረሱን በመጥቀስ አሁን ላይ ከ4 ሚሊዬዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል።
የአፈር ማዳበሪያውን ከማጓጓዝ ጎን ለጎን የአርሶ አደሩን አቅም ባገናዘበ መልኩ የማስራጨት ስራ ይከናወናል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025