
አዲስ አበባ፤የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሺዴ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እና የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በኢትዮጵያ ቆይታቸው፥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፖሊሲዎች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ክሪስታሊና ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድ እና ኢኮኖሚ እድሎች አስመልክቶ ሀሳቦችን እንደሚለዋወጡም ገልጿል።
የዋና ዳይሬክተሯ ጉብኝት አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ልማት ለመደገፍ እና የፖሊሲ ምክክሮችን በማድረግ የማይበገር፣ የጋራ እና ዘላቂነት ያለው ብልጽግና እንደሚመጣ ያለውን ቁርጠኝነት ያመላክታል ተብሏል።
ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ እ.አ.አ በ2019 በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ በመረጃው አስታውሷል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026