አዲስ አበባ፤የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል እያደረገ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፥ኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያስገነባውን የፕላስቲክ ፎርምወርክ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ለአምራች ኢንዱስትሪ በልዩ ትኩረት የፖሊሲ እና የህግ ማእቀፎችን በማሻሻል ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግ መቻሉንም ገልጸዋል።
በቀጣይም የዘርፉን ምርትና ምርታማነት በማጎልበት ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርትን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ መገንባት የሚቻለው ወደ ሀገር የሚገባ ምርትን የሚተኩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካም ተኪ ምርትን በማስፋትና የሀገራዊ ፖሊሲን በማሳካት ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
ፋብሪካው በኢትዮጵያ የእንጨት ፎርምዎርኮችን በፕላስቲክ መተካት መቻሉ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከመደገፍ አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል።
በተለይም የደን ጭፍጨፋን የሚታደግ እና የግንባታ ዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚጨምር መሆኑንም አመላክተዋል።
ኢንዱስትሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚና ባለቤት ካሳነሽ አያሌው በበኩላቸው፥ ፋብሪካው በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የግንባታ ፕላስቲክ ፎርምዎርክ አምርቶ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እየተከለች ቢሆንም በሌላ በኩል ለእንጨት ፎርምዎርክ መስሪያ ዛፎች እንደሚቆረጡ አንስተዋል።
የፕላስቲክ ፎርምዎርኩ ከእንጨት የሚሰራ የግንባታ ግብዓትን በመተካት የደን መጨፍጨፍን ለመቀነስ እንደሚያግዝም ጠቁመዋል።
ፋብሪካው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪን ማዳን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025