አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፦ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ክህሎት መር የሰብል ምርታማነትን ባህል የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
በአዳማ ከተማ ለፌዴራልና ክልሎች የስራ ኃላፊዎችና ሙያተኞች በሰብል አመራረት ፓኬጅ፣ ግብርና ኤክስቴንሽን፣ የአፈር ለምነትና የኩታ ገጠም አስተራረስ ዘዴ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ መለስ መኮንን(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የሰብል ምርታማነት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የወጪ ንግድን በመጠንና በጥራት ማምረት፣ ገቢ የኢንዱስትሪ ግብዓትን መተካትና የስራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ ያስቻሉ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
የግብርና ዕድገትን ለማሳለጥ ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ለአርሶ አደሮች ስልጠናዎችን በመስጠት የተሰናሰለ እና ዘመናዊ የምርታማነት ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በዚህም የግብርና ምርታማነት ስኬቶችን በማስቀጠል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት ክህሎት መር የሰብል ምርታማነትን ባህል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ በሪሶ ፈይሳ፤ ሀገራዊ ለውጡ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ እመርታዊ ዕድገት ማስመዝገብ ያስቻሉ የማሻሻያ እርምጃዎች የተወሰዱበት መሆኑን ገልጸዋል።
በዚሁ መነሻነትም በክልሉ በሁሉም የግብርና ምርታማነት መስክ ከዝግጅት እስከ ምርት ስብሰባ ድረስ ስኬታማ እርምጃዎችን በመውሰድ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው፤ የክልሉን የሰብል ልማት አቅም ታሳቢ በማድረግ በኩታ ገጠምና ሜካናይዜሽን እርሻ ልማት ስኬታማ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑም ለምግብነት፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት እና ወጪ ንግድ ጉልህ ፋይዳ ያላቸው ሰብሎችን በማልማት በምግብ እራስን የመቻል ሀገራዊ ግብ ማሳካት ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እያሱ አብርሃ(ዶ/ር)፤ በሁሉም የግብርና ልማት መስክ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ያስቻሉ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።
የፌዴራል መንግስትና ባለድርሻ አካላት የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ግብዓት አቅርቦት ላይ ያደረጉት ድጋፍ የሰብል ምርታማነት፣ ጥራትና ተወዳዳሪነት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዓለም-ይርጋ ወልደ-ሥላሴ፤ በክልሉ የግብርና ምርታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እመርታዊ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
"የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሰብል ምርታማነትን ማሳደግ" በሚል መሪ ሃሳብ የተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠናም የእርሻና ሆርቲካልቸር ምርታማነትን የሚያሳድጉ አሰራሮችን በመዘርጋት ዘመናዊ የሰብል፣ የመስኖ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት፣ የእፅዋት ጥበቃና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ስራዎችን ለማስፋፋት ጉለህ አበርክቶ እንደሚኖረው ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025