ባህርዳር፤ የካቲት 3/2017(ኢዜአ)፡- የብልጽግና ፓርቲ በ2ኛው ጉባኤ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተሳለጠና ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በተከናወኑ ተግባራትና በ2ኛው ጉባኤ አቅጣጫዎች ላይ ማምሻውን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወይዘሮ ባንቻምላክ ገብረ ማሪያም መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በመጀመሪያው ጉባኤ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ነጻና ገለልተኛ በሆነ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ ተቀምጦ እንደነበር አስታውሰዋል።
በዚህም የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ መንስኤና የመፍትሄ አቅጣጫ የሚያመላክት ጥናት እስከ ወረዳ ድረስ መከናወኑን ገልጸዋል።
የመጀመሪያው የፓርቲው ጉባኤ የትግበራ ጊዜ ሲቪል ሰርቪሱን ለማዘመን እንደ ዝግጅት ምዕራፍ መወሰዱን ጠቁመው በቀጣይ የጥናቱን ግኝት መሰረት በማድረግ ወደ ተግባር ይገባል ብለዋል።
ለዚህም የብልጽግና ፓርቲ በ2ኛው ጉባኤ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተሳለጠና ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በተለይም በየተቋማቱ ያለውን ሰራተኛ የአቅም ክፍተት መሙላት የሚያስችል ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው ከዚህ ጎን ለጎንም ተጠያቂነትን ለማስፈን ይሰራል ነው ያሉት።
በክልሉ ያለውን የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማቃለል በሚያስችል መልኩ እንደሚፈጸምም በመግለጫቸው አመላክተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...
Feb 28, 2025
ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...
Feb 24, 2025
አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...
Feb 12, 2025