
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት አፍሪካ በምግብ ራሷን እንደምትችል ማረጋገጫ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።
ዓለም አቀፍ የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የአየር ንብረት ለውጥና የምግብ ዋስትና ችግር እየተባባሰ መሆኑን ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ማህብረሰብ አቀፍ የግብርና ልማት ሽግግርን እየመራች ነው ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምን ታሳቢ ያደረጉ የምግብ ምርታማነት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗን ጠቅሰው፥ ለአብነትም የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርን ጠቅሰዋል።
በዚህ መርሐግብር 40 ቢሊዮን ችግኝ መትከላችን ብቻ የደን ሽፋንን ከማሳደጉም በላይ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ዋስትናቸውን እያረጋገጡ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ሌላኛው የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ኢኒሼቲቭ የስንዴ ልማት መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህም የሚገባ ስንዴን በማቆም የስንዴ ምርት ፍጆታዋን በራሷ አቅም ማምረት ችላለች ብለዋል።
ይህም አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል ማረጋገጫ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ለመስኖ፣ ለሜካናይዜሽንና ሌሎች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የግብርና ስርዓቶች ትኩረት በመስጠት የምግብ ሉዓላዊነቷን ታረጋግጣለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ የሌማት ትሩፋትን በመጀመር በቤተሰብ ደረጃ የተመጣጠነ የምግብ ስርዓትን የሚያረጋግጡ የወተት፣ የእንቁላል፣ የማርና ሌሎችንም ምርቶች ላይ በማተኮር ውጤታማ ስራዎችን እየሰራች መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አፍሪካም ሌማቷን መሙላት የሚያስችላት አቅም አላት ያሉት ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ለአህጉሪቱ የሚተርፍ እንደሆነም አንስተዋል።
በመስኖ ልማትም በርካታ የግብርና ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ አርብቶ አደሮችን ጭምር ወደዚህ መርሐግብር ማሳተፍ ተችሏል ነው ያሉት።
የመስኖ ፕሮጀክቶቻችን የምግብ ዋስትናንና የማይበገር የግብርና ስርዓት መገንባትን ዓላማ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።
አፍሪካውያን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለመስኖ ልማት፣ ለግብርና ኢንቨስትመንት፣ ለቴክኖሎጂና ለመረጃ ጥራት ትኩረት እንዲሰጡም ጠይቀዋል።
አፍሪካውያን በጋራ ከሰሩ ርሃብን ማስወገድ፣ የአየር ንብረት ለውጥን በብቃት መቋቋምና የትውልዱን የብልፅግና መሻትን ማሳካት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026