
ሽረ እንዳስላሴ የካቲት 05/2017 (ኢዜአ)- የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በጥናት ያገኛቸውን የምርምር ውጤቶች አገልግሎት ላይ እንዲውሉ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሽረ እንዳስላሴ ካምፓስ ኃላፊ ዳዊት ማሞ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩ ባለፈ ማህበራዊ አገልግሎቱን እየተወጣና ችግር ፈች የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርምር ስራዎቹ አነስተኛ የወርቅ ማጠቢያ መሳሪያና አደገኛ አረምን ወደ ከሰል የሚቀይር አዲስ የፈጠራ ውጤት ይፋ አድርጓል።
በዚህም በምርምር የተገኘው የወርቅ ማጠቢያ ማሽን በሰው ጉልበት ሲከናወን የቆየውን የወርቅ ማእድን ከአፈር የመለየት እና የማጠብ ስራ ፈጣንና ቀልጣፋ የሚያደርግ ስለመሆኑ ሃላፊው አንስተዋል።
የማሽኑ አገልግሎት ከፍተኛ በመሆኑ በአንድ ሰዓት ከግማሽ ኩንታል አፈር ውስጥ ያለምንም ብክነት የወርቅ ማእድንን መለየትና ማጠብ ያስችላል ብለዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋለውን አደገኛ አረም በኬሚካል ወደ ከሰል ምርትነት መለወጥ የሚያስችል ግኝትም ሌላኛው የዩኒቨርሲቲው ውጤት መሆኑን አንስተዋል።
እነዚህ ፈጠራዎች በሙከራ ደረጃ ውጤታማ መሆናቸውን አስታውሰው በቀጣይ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በቀጣይም የአፈርን ለምነት ለመጠበቅ የሚያስችል ''ቨርሚንግ'' የተባለ ኮምፖስት ለማምረት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ዳዊት ተናግረዋል።
የምርምር ስራዎቹ በዩኒቨርሲቲው እውቅና የተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በህብርተሰቡ ዘንድ ጥቅም ላይ ለማዋል ይሰራል ብለዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026